PDF Print E-mail

 የኮሚሽነሩ መልዕክት

 አቶ ተስፋዬ ኦሜጋ ፋልታሞ,

ato-tesfaya1

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የከተማዋን ልማትና የመልካም አስተዳደር ችግሮች በመፈታት ህብረተሰቡ በልማቱ ተጠቃሚ እንዲሆን ለማስቻል ትርጉም ያለው ተግባር እያናከናወነ መሆኑ ይታወቃል፡፡ በመሆኑም መንግስት ያወጣውን የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ተግባራዊ ለማድረግና የሚፈለገውን ልማትና የህዝቡን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ሁሉም አካል በተሰማራበት የሙያ መስክ ጠንክሮ መስራት እንዲሚጠበቅበት ይታመናል፡፡

በአዲስ አበባ ከተማም የነዋሪዋን መሠረታዊ ፍላጐትና ጥያቄ መሠረት ያደረገ ሥር-ነቀል ተቋማዊ የአሠራር ለውጥ በማምጣት ለህዝቡ ጥያቄ ፈጣን ምላሽ ለመስጠት የሚያስችሉ አሠራሮችን በማሳደግ፣ በዘመናዊ ቴክኖሎጂ የተደገፈ የመረጃ አስተዳዳር ስርዓት በመዘርጋት፣ ቀልጣፋና ተገልጋይ ተኮር አገልግሎት አሰጣጥ ስርዓትን እውን ማድረግ ያስፈልጋል፡፡ ከዚህ አንፃር የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ስፖርት ኮሚሽንም ከተቋቋመበት ዓላማ አንፃር በስፖርት ፖሊሲና እቅዶች፣ መመሪያዎችና ደንቦች እንዲሁም በኮሚሽኑ በሚሰጡ አገልግሎቶች ዙሪያ ተገልጋዩ ትክክለኛ፣ ወቅታዊና ግልጽ መረጃ እንዲኖረው በማድረግ፣ በህዝብና በመንግስት ሥራዎች ላይ በበቂ ሁኔታ  እንዲሳተፍ ማድረግ ያስፈልጋል፡፡ ከዚህም ሌላ ከኮሚሽኑ የሚያገኘውን አገልግሎት አውቆ እውቀቱን፣ ገንዘቡንና መላ አቅሙን ለስፖርት ልማት እንዲያውል አሰራራችንን ግልጽና አሳታፊ ለማድረግ እንዲቻል በዘመናዊ ቴክኖሎጂ መደገፍ አስፈላጊ ነው፡፡ በመሆኑም ከተማ አስተዳደራችን የየሴክተሩ መ/ቤቶች አገልግሎት አስጣጥ ለተገልጋዩ ቀልጣፋና ተደራሽ እንዲሆን በሰጠው ከፍተኛ ትኩረት ሴክተሮች አቅማቸው በዘመናዊ አሠራር እንዲደገፍ እያደረገ ይገኛል፡፡ ከዚህ አንፃር የአዲስ አበባ ከተማ ስፖርት ኮሚሽንም የህብረተሰቡን የስፖርት መረጃ ፍላጐት ለማርካት ይቻል ዘንድ የኮሚሽኑን ድህረ-ገፁ በመክፈት ለተገልጋዩ ክፍት እንዲሆን ተደርጓል፡፡ በመሆኑም የኮሚሽናችን ተገልጋዩችና መላሙ የከተማዋ ነዋሪዎች ማንኛውንም የዘርፍን መረጃ ለማግኘትም ሆነ ለመስጠት የሚያስችል ምቹ ሁኔታ የተፈጠረ በመሆኑ በዚህ ድህረ-ገጽ በስፋት መጠቀም የምትችሉ መሆኑን እያሳውኩ ለድህረ-ገጽ መከፈት አስፈላጊውን እገዛ ላደረገልን የከተማችን አስተዳደርና ባለሙያዎች በኮሚሽኑ ስም ምስጋናዬን አቀርባለሁ፡፡


በቀጣይም ኮሚሽናችን የስፖርት አደረጃጀታችን ህዝባዊ መሠረት እንዲኖረው የስፖርት ማዘውተሪያ ሥፍራዎችን ለማልማትና ለማስፋፋት፣ ህብረተሰቡ በስፖርት ተሳትፊና ተጠቃሚ ለማድረግ፣ የስፖርት ባለሙያዎችን በብዛትና በጥረት ለማሰልጠን፣ ምርጥና ተተኪ ስፖርተኞችን ለማፍራት ከዘመኑ ሥልጣኔ ጋር የተጠጣመ ቀልጣፋና ተጠያቂነት የሰፈነበት አገልግሎት በመስጠት የከተማችን ብሎም የአገራችንን የስፖርት ህዳሴ ለማምጣት እጅ ለዕጅ ተያይዘንና ተደጋግፈን በመስራት አገራችን በአህጉርና በዓለም አቀፍ ውድድሮች ተገቢውን ደረጃ እንድታገኝ ብሎም ጤናማና አምራች ተተኪ ትውልድ ለመፍጠር በጋራ እንድንነሳ ጥሪዬን አቀርባለሁ፡፡
አመሰግናለሁ!!


  

የቅርብ ዜና

የአዲስ አበባ ከተማ ስፖርት ኮሚሽን በቅርቡ አዲስ ድህረ-ገፅ ለቀቀ

 

 የአዲስ አበባ ከተማ ስፖርት ኮሚሽን በቅርቡ አዲስ ድህረ-ገፅ በሚከተለው አድራሻ ለቀቀ www.aasc.gov.et፡፡ ይህ ዌብ ሳት ኮሚሽኑን በማስተዋወቅና የተለያዩ ዜናዎችን በማቅረብ ከፍተኛ ሚና ይጫወታል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

 

እየተጠቀሙ ያሉ

We have 1 guest online

የስፖርት ማዕከላት